ማርቆስ 16:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ሰንበት+ ካለፈ በኋላም መግደላዊቷ ማርያም፣ የያዕቆብ እናት ማርያምና+ ሰሎሜ ሄደው አስከሬኑን ሊቀቡ ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞች ገዙ።+ ሉቃስ 23:55, 56 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 55 ከገሊላ ከኢየሱስ ጋር አብረው የመጡት ሴቶች ግን ተከትለው በመሄድ መቃብሩን አዩ፤ አስከሬኑም እንዴት እንዳረፈ ተመለከቱ።+ 56 ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞችና ዘይቶች ለማዘጋጀትም ተመልሰው ሄዱ። ሆኖም ሕጉ በሚያዘው መሠረት በሰንበት አረፉ።+ ዮሐንስ 19:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 የኢየሱስንም አስከሬን ወስደው በአይሁዳውያን የአገናነዝ ልማድ መሠረት ጥሩ መዓዛ ባላቸው በእነዚህ ቅመሞች ተጠቅመው በበፍታ ጨርቅ ገነዙት።+
55 ከገሊላ ከኢየሱስ ጋር አብረው የመጡት ሴቶች ግን ተከትለው በመሄድ መቃብሩን አዩ፤ አስከሬኑም እንዴት እንዳረፈ ተመለከቱ።+ 56 ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞችና ዘይቶች ለማዘጋጀትም ተመልሰው ሄዱ። ሆኖም ሕጉ በሚያዘው መሠረት በሰንበት አረፉ።+