-
2 ዜና መዋዕል 17:3-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ኢዮሳፍጥ፣ በቀድሞዎቹ ዘመናት አባቱ ዳዊት የሄደበትን መንገድ በመከተሉና+ ባአልን ባለመፈለጉ ይሖዋ ከእሱ ጋር ነበር። 4 የእስራኤልን ልማድ ከመከተል ይልቅ+ የአባቱን አምላክ ፈልጓል፤+ ትእዛዙንም ተከትሏል።* 5 ይሖዋ መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤+ የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ለኢዮሳፍጥ ስጦታ ያመጡለት ነበር፤ እሱም ብዙ ሀብትና ታላቅ ክብር አገኘ።+ 6 ልቡም የይሖዋን መንገዶች በድፍረት ተከተለ፤ ደግሞም ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎችና የማምለኪያ ግንዶቹን* ከይሁዳ አስወገደ።+
-