ዘፍጥረት 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋም ለአብራም ተገለጠለትና “ይህችን ምድር ለዘርህ+ እሰጣለሁ”+ አለው። ስለዚህ አብራም ተገልጦለት ለነበረው ለይሖዋ በዚያ መሠዊያ ሠራ። ነህምያ 9:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አብራምን+ መርጠህ ከከለዳውያን ዑር+ ያወጣኸውና አብርሃም+ ብለህ የጠራኸው እውነተኛው አምላክ ይሖዋ አንተ ነህ። 8 ልቡ በፊትህ ታማኝ ሆኖ ስላገኘኸው+ የከነአናውያንን፣ የሂታውያንን፣ የአሞራውያንን፣ የፈሪዛውያንን፣ የኢያቡሳውያንንና የገርጌሻውያንን ምድር ለእሱ ይኸውም ለዘሩ ለመስጠት ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን ተጋባህ፤+ ጻድቅ ስለሆንክም ቃልህን ጠበቅክ። ኢሳይያስ 41:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግን አገልጋዬ ነህ፤+ያዕቆብ ሆይ፣ አንተን መርጬሃለሁ፤+የወዳጄ የአብርሃም ዘር ነህ፤+ ያዕቆብ 2:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ደግሞም “አብርሃም በይሖዋ* አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት”+ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፤ እሱም የይሖዋ* ወዳጅ ለመባል በቃ።+
7 አብራምን+ መርጠህ ከከለዳውያን ዑር+ ያወጣኸውና አብርሃም+ ብለህ የጠራኸው እውነተኛው አምላክ ይሖዋ አንተ ነህ። 8 ልቡ በፊትህ ታማኝ ሆኖ ስላገኘኸው+ የከነአናውያንን፣ የሂታውያንን፣ የአሞራውያንን፣ የፈሪዛውያንን፣ የኢያቡሳውያንንና የገርጌሻውያንን ምድር ለእሱ ይኸውም ለዘሩ ለመስጠት ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን ተጋባህ፤+ ጻድቅ ስለሆንክም ቃልህን ጠበቅክ።
8 “እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግን አገልጋዬ ነህ፤+ያዕቆብ ሆይ፣ አንተን መርጬሃለሁ፤+የወዳጄ የአብርሃም ዘር ነህ፤+ ያዕቆብ 2:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ደግሞም “አብርሃም በይሖዋ* አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት”+ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፤ እሱም የይሖዋ* ወዳጅ ለመባል በቃ።+