መሳፍንት 11:27, 28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 እንግዲህ እኔ ምንም የበደልኩህ ነገር የለም፤ አንተም ብትሆን በእኔ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መነሳትህ ተገቢ አይደለም። ፈራጁ ይሖዋ+ በእስራኤል ሕዝብና በአሞን ሕዝብ መካከል ዛሬ ይፍረድ።’” 28 የአሞናውያን ንጉሥ ግን ዮፍታሔ የላከበትን መልእክት ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም። መዝሙር 7:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ ተነስ፤በእኔ ላይ በቁጣ በሚገነፍሉት ጠላቶቼ ላይ ተነስ፤+ለእኔ ስትል ንቃ፤ ፍትሕ እንዲሰፍንም እዘዝ።+
27 እንግዲህ እኔ ምንም የበደልኩህ ነገር የለም፤ አንተም ብትሆን በእኔ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መነሳትህ ተገቢ አይደለም። ፈራጁ ይሖዋ+ በእስራኤል ሕዝብና በአሞን ሕዝብ መካከል ዛሬ ይፍረድ።’” 28 የአሞናውያን ንጉሥ ግን ዮፍታሔ የላከበትን መልእክት ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም።