2 ነገሥት 17:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሖዋ በነቢያቱ ሁሉና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ+ አማካኝነት እስራኤልንና ይሁዳን “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ!+ አባቶቻችሁን ባዘዝኳቸውና በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ለእናንተ በሰጠሁት ሕግ መሠረት ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ጠብቁ” በማለት በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 14 እነሱ ግን አልሰሙም፤ በአምላካቸው በይሖዋ እንዳላመኑት አባቶቻቸው እነሱም ግትሮች ሆኑ።*+ 2 ዜና መዋዕል 36:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር። ኤርምያስ 7:25, 26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 አባቶቻችሁ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህ ቀን ድረስ ይህን አደረጉ።+ በመሆኑም አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያት ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ ደግሜ ደጋግሜ በየዕለቱ* ላክኋቸው።+ 26 እነሱ ግን እኔን ለመስማት እንቢተኛ ሆኑ፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም።+ ይልቁንም ግትር ሆኑ፤* አባቶቻቸው ከሠሩት የከፋ ነገር አደረጉ!
13 ይሖዋ በነቢያቱ ሁሉና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ+ አማካኝነት እስራኤልንና ይሁዳን “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ!+ አባቶቻችሁን ባዘዝኳቸውና በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ለእናንተ በሰጠሁት ሕግ መሠረት ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ጠብቁ” በማለት በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 14 እነሱ ግን አልሰሙም፤ በአምላካቸው በይሖዋ እንዳላመኑት አባቶቻቸው እነሱም ግትሮች ሆኑ።*+
15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር።
25 አባቶቻችሁ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህ ቀን ድረስ ይህን አደረጉ።+ በመሆኑም አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያት ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ ደግሜ ደጋግሜ በየዕለቱ* ላክኋቸው።+ 26 እነሱ ግን እኔን ለመስማት እንቢተኛ ሆኑ፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም።+ ይልቁንም ግትር ሆኑ፤* አባቶቻቸው ከሠሩት የከፋ ነገር አደረጉ!