ዘፀአት 20:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከእኔ በቀር* ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።+ ዘፀአት 20:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 አትስገድላቸው፤ ተታለህም እነሱን አታገልግል፤+ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና+ በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤ ዘዳግም 7:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች በእሳት አቃጥሉ።+ ወጥመድ ሊሆንብህ ስለሚችል በእነሱ ላይ ያለውን ብርም ሆነ ወርቅ አትመኝ ወይም ለራስህ አትውሰድ፤+ ምክንያቱም ይህ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነገር ነው።+ 2 ዜና መዋዕል 28:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ንጉሥ አካዝ በተጨነቀ ጊዜ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት መፈጸሙን ይበልጥ ገፋበት። 23 እሱም “የሶርያ ነገሥታት አማልክት እነሱን ስለሚረዷቸው፣ እኔንም እንዲረዱኝ መሥዋዕት አቀርብላቸዋለሁ”+ በማለት ላሸነፉት+ የደማስቆ አማልክት+ መሥዋዕት ያቀርብ ጀመር። ይሁንና እነሱ፣ ለእሱም ሆነ ለመላው እስራኤል እንቅፋት ሆኑ።
5 አትስገድላቸው፤ ተታለህም እነሱን አታገልግል፤+ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና+ በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤
25 የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች በእሳት አቃጥሉ።+ ወጥመድ ሊሆንብህ ስለሚችል በእነሱ ላይ ያለውን ብርም ሆነ ወርቅ አትመኝ ወይም ለራስህ አትውሰድ፤+ ምክንያቱም ይህ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነገር ነው።+
22 ንጉሥ አካዝ በተጨነቀ ጊዜ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት መፈጸሙን ይበልጥ ገፋበት። 23 እሱም “የሶርያ ነገሥታት አማልክት እነሱን ስለሚረዷቸው፣ እኔንም እንዲረዱኝ መሥዋዕት አቀርብላቸዋለሁ”+ በማለት ላሸነፉት+ የደማስቆ አማልክት+ መሥዋዕት ያቀርብ ጀመር። ይሁንና እነሱ፣ ለእሱም ሆነ ለመላው እስራኤል እንቅፋት ሆኑ።