2 ዜና መዋዕል 14:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የይሁዳንም ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “እነዚህን ከተሞች እንገንባ፤ በዙሪያቸውም ቅጥርና ማማዎች+ እንዲሁም በሮችና* መቀርቀሪያዎች እንሥራ። አምላካችንን ይሖዋን ስለፈለግነው ምድሪቱ አሁንም በእጃችን ናት። እኛ ፈልገነዋል፤ እሱም በዙሪያችን ካሉት ጠላቶቻችን ሁሉ እረፍት ሰጥቶናል።” በመሆኑም የግንባታ ሥራቸው ስኬታማ ሆነ።+ መዝሙር 1:2, 3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይልቁንም በይሖዋ ሕግ ደስ ይለዋል፤+ሕጉንም በቀንና በሌሊት በለሆሳስ ያነበዋል።*+ 3 በጅረቶች ዳር እንደተተከለ፣ፍሬውን በወቅቱ እንደሚሰጥ፣ቅጠሉም እንደማይጠወልግ ዛፍ ይሆናል። የሚሠራውም ሁሉ ይሳካለታል።+
7 የይሁዳንም ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “እነዚህን ከተሞች እንገንባ፤ በዙሪያቸውም ቅጥርና ማማዎች+ እንዲሁም በሮችና* መቀርቀሪያዎች እንሥራ። አምላካችንን ይሖዋን ስለፈለግነው ምድሪቱ አሁንም በእጃችን ናት። እኛ ፈልገነዋል፤ እሱም በዙሪያችን ካሉት ጠላቶቻችን ሁሉ እረፍት ሰጥቶናል።” በመሆኑም የግንባታ ሥራቸው ስኬታማ ሆነ።+
2 ይልቁንም በይሖዋ ሕግ ደስ ይለዋል፤+ሕጉንም በቀንና በሌሊት በለሆሳስ ያነበዋል።*+ 3 በጅረቶች ዳር እንደተተከለ፣ፍሬውን በወቅቱ እንደሚሰጥ፣ቅጠሉም እንደማይጠወልግ ዛፍ ይሆናል። የሚሠራውም ሁሉ ይሳካለታል።+