-
1 ዜና መዋዕል 23:27-30አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት ከሌዊ ልጆች መካከል የተቆጠሩት 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች እነዚህ ነበሩ። 28 የሌዋውያኑ ተግባር በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ይኸውም ቅጥር ግቢዎቹንና+ የመመገቢያ ክፍሎቹን፣ ቅዱስ የሆነውን ነገር ሁሉ የማንጻቱን ሥራና በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚከናወኑትን አስፈላጊ ሥራዎች ሁሉ ኃላፊነት ወስደው በመሥራት የአሮንን ልጆች+ መርዳት ነበር። 29 ደግሞም የሚነባበረውን ዳቦ፣*+ ለእህል መባ የሚያገለግለውን የላመ ዱቄት፣ እርሾ ያልገባበትን ስስ ቂጣ፣+ በምጣድ የሚጋገረውን ቂጣና በዘይት የሚለወሰውን ሊጥ+ በማዘጋጀት እንዲሁም ከሁሉም ዓይነት መለኪያዎችና መስፈሪያዎች ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በማከናወን ያግዟቸው ነበር። 30 ለይሖዋ ምስጋናና ውዳሴ ለማቅረብ ጠዋት ጠዋትም+ ሆነ ማታ ማታ+ ይቆሙ ነበር።
-