34 “ዘመኑ በተፈጸመ ጊዜ+ እኔ ናቡከደነጾር ወደ ሰማያት ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑሉንም አምላክ አመሰገንኩ፤ ለዘላለም የሚኖረውንም አወደስኩ፤ አከበርኩትም፤ ምክንያቱም የመግዛት ሥልጣኑ ዘላለማዊ ነው፤ መንግሥቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።+ 35 የምድር ነዋሪዎች ሁሉ እንደ ኢምንት ይቆጠራሉ፤ በሰማያት ሠራዊትና በምድር ነዋሪዎች ላይ እንደ ፈቃዱ ያደርጋል። ሊያግደው ወይም ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ብሎ ሊጠይቀው የሚችል ማንም የለም።+