1 ዜና መዋዕል 6:31, 32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ዳዊት፣ ታቦቱ በይሖዋ ቤት ከተቀመጠ በኋላ በዚያ የሚዘመረውን መዝሙር እንዲመሩ የሾማቸው እነዚህ ነበሩ።+ 32 እነሱ ሰለሞን የይሖዋን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪገነባ+ ድረስ በማደሪያ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ከመዝሙር ጋር የተያያዘ ኃላፊነት ተሰጣቸው፤ በተሰጣቸውም ኃላፊነት መሠረት አገልግሎታቸውን ያከናውኑ ነበር።+ 1 ዜና መዋዕል 23:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ደግሞም 4,000 በር ጠባቂዎች+ እንዲሁም ዳዊት “ውዳሴ ለማቅረብ የሠራኋቸው ናቸው” ባላቸው መሣሪያዎች ለይሖዋ ውዳሴ+ የሚያቀርቡ 4,000 ሰዎች ነበሩ። 1 ዜና መዋዕል 25:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 በተጨማሪም ዳዊትና የአገልግሎት ቡድኖቹ አለቆች በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎችና+ በሲምባል+ ትንቢት በመናገር እንዲያገለግሉ ከአሳፍ፣ ከሄማን እና ከየዱቱን+ ወንዶች ልጆች መካከል አንዳንዶቹን ለዩ። ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑት ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦
31 ዳዊት፣ ታቦቱ በይሖዋ ቤት ከተቀመጠ በኋላ በዚያ የሚዘመረውን መዝሙር እንዲመሩ የሾማቸው እነዚህ ነበሩ።+ 32 እነሱ ሰለሞን የይሖዋን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪገነባ+ ድረስ በማደሪያ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ከመዝሙር ጋር የተያያዘ ኃላፊነት ተሰጣቸው፤ በተሰጣቸውም ኃላፊነት መሠረት አገልግሎታቸውን ያከናውኑ ነበር።+
25 በተጨማሪም ዳዊትና የአገልግሎት ቡድኖቹ አለቆች በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎችና+ በሲምባል+ ትንቢት በመናገር እንዲያገለግሉ ከአሳፍ፣ ከሄማን እና ከየዱቱን+ ወንዶች ልጆች መካከል አንዳንዶቹን ለዩ። ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑት ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦