-
አስቴር 7:4-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 እኔና ሕዝቤ ለጥፋት፣ ለመገደልና ለመደምሰስ+ ተሸጠናልና።+ የተሸጥነው ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች እንድንሆን ብቻ ቢሆን ኖሮ ዝም ባልኩ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ጥፋት በንጉሡም ላይ ጉዳት ስለሚያስከትል በቸልታ መታለፍ የለበትም።”
5 ንጉሥ አሐሽዌሮስም ንግሥት አስቴርን “ለመሆኑ ይህ ሰው ማን ነው? እንዲህ ያለውን ነገር ለማድረግ የደፈረውስ ሰው የታለ?” አላት። 6 አስቴርም “ባላጋራና ጠላት የሆነው ሰው ይህ ክፉው ሃማ ነው” አለች።
ሃማም በንጉሡና በንግሥቲቱ ፊት በፍርሃት ተንቀጠቀጠ።
-