6 የእውነተኛው አምላክ ልጆች+ በይሖዋ ፊት ለመቆም+ የሚገቡበት ቀን በደረሰ ጊዜ ሰይጣንም+ መጥቶ በመካከላቸው ቆመ።+
7 ከዚያም ይሖዋ ሰይጣንን “ከየት መጣህ?” አለው። ሰይጣንም “በምድር ሁሉ ላይ ስዞርና በእሷ ላይ ስመላለስ ቆይቼ መጣሁ”+ ሲል ለይሖዋ መለሰ። 8 ይሖዋም ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትከው? በምድር ላይ እንደ እሱ ያለ ሰው የለም። በንጹሕ አቋም የሚመላለስ ቅን ሰው+ እንዲሁም አምላክን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ነው።”