መዝሙር 139:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ፤በመቃብር* አልጋዬን ባነጥፍም እነሆ፣ አንተ በዚያ ትኖራለህ።+ ዕብራውያን 4:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ደግሞም ከአምላክ እይታ የተሰወረ አንድም ፍጥረት የለም፤+ ይልቁንም ተጠያቂዎች በሆንበት+ በእሱ ዓይኖች ፊት ሁሉም ነገር የተራቆተና ገሃድ የወጣ ነው።