መዝሙር 146:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 መንፈሱ* ትወጣለች፤ ወደ መሬት ይመለሳል፤+በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።+ መክብብ 9:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኃይልህ አከናውን፤ አንተ በምትሄድበት በመቃብር* ሥራም ሆነ ዕቅድ፣ እውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።+ ኢሳይያስ 57:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 57 ጻድቁ ሞቷል፤ይህን ግን ማንም ልብ አይልም። ታማኝ ሰዎች ተወስደዋል፤*+ሆኖም ጻድቁ የተወሰደውከመከራ የተነሳ እንደሆነ* የሚያስተውል የለም። 2 እሱ ሰላም ያገኛል። በቅንነት የሚሄዱ ሁሉ አልጋቸው* ላይ ያርፋሉ።
57 ጻድቁ ሞቷል፤ይህን ግን ማንም ልብ አይልም። ታማኝ ሰዎች ተወስደዋል፤*+ሆኖም ጻድቁ የተወሰደውከመከራ የተነሳ እንደሆነ* የሚያስተውል የለም። 2 እሱ ሰላም ያገኛል። በቅንነት የሚሄዱ ሁሉ አልጋቸው* ላይ ያርፋሉ።