2 ሳሙኤል 12:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከዚያም ዳዊት ናታንን “በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁ” አለው።+ ናታንም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ይሖዋም ኃጢአትህን ይቅር ይላል።*+ አትሞትም።+ መዝሙር 32:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በመጨረሻ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ስህተቴን አልሸፋፈንኩም።+ “የፈጸምኳቸውን በደሎች ለይሖዋ እናዘዛለሁ” አልኩ።+ አንተም ስህተቴንና ኃጢአቴን ይቅር አልክ።+ (ሴላ) ምሳሌ 28:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 የሠራውን በደል የሚሸፋፍን አይሳካለትም፤+የሚናዘዝና የሚተወው ሁሉ ግን ምሕረት ያገኛል።+ ሉቃስ 15:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ከዚያም ልጁ ‘አባቴ ሆይ፣ በአምላክና በአንተ ላይ በደል ፈጽሜአለሁ።+ ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም’ አለው። 1 ዮሐንስ 1:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ኃጢአታችንን የምንናዘዝ ከሆነ እሱ ታማኝና ጻድቅ ስለሆነ ኃጢአታችንን ይቅር ይለናል፤ እንዲሁም ከክፋት ሁሉ ያነጻናል።+
5 በመጨረሻ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ስህተቴን አልሸፋፈንኩም።+ “የፈጸምኳቸውን በደሎች ለይሖዋ እናዘዛለሁ” አልኩ።+ አንተም ስህተቴንና ኃጢአቴን ይቅር አልክ።+ (ሴላ)