ምሳሌ 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በራስህ አመለካከት ጥበበኛ አትሁን።+ ይሖዋን ፍራ፤ ከክፉም ራቅ። ማቴዎስ 11:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ።+ ሮም 11:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 እውነት ነው! እነሱ ባለማመናቸው ተሰብረዋል፤+ አንተ ግን በእምነት ቆመሃል።+ ቢሆንም መፍራት እንጂ መታበይ አይገባህም። ሮም 12:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ለራሳችሁ ያላችሁ ዓይነት አመለካከት ለሌሎችም ይኑራችሁ፤ የትዕቢት ዝንባሌ እንዳያድርባችሁ ተጠንቀቁ፤ ትሕትና የሚንጸባረቅበት አስተሳሰብ ይኑራችሁ።+ ጥበበኞች እንደሆናችሁ አድርጋችሁ አታስቡ።+ 1 ቆሮንቶስ 1:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ወንድሞች፣ ከራሳችሁ ሁኔታ መረዳት እንደምትችሉት በሰብዓዊ አመለካከት* ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፣+ ኃያላን የሆኑ ብዙዎች እንዲሁም ከትልቅ ቤተሰብ የተወለዱ ብዙዎች አልተጠሩም፤+
25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ።+
16 ለራሳችሁ ያላችሁ ዓይነት አመለካከት ለሌሎችም ይኑራችሁ፤ የትዕቢት ዝንባሌ እንዳያድርባችሁ ተጠንቀቁ፤ ትሕትና የሚንጸባረቅበት አስተሳሰብ ይኑራችሁ።+ ጥበበኞች እንደሆናችሁ አድርጋችሁ አታስቡ።+
26 ወንድሞች፣ ከራሳችሁ ሁኔታ መረዳት እንደምትችሉት በሰብዓዊ አመለካከት* ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፣+ ኃያላን የሆኑ ብዙዎች እንዲሁም ከትልቅ ቤተሰብ የተወለዱ ብዙዎች አልተጠሩም፤+