24 ደግሞም ‘ከመካከላችን ታላቅ የሆነው ማን ነው?’ በሚል በመካከላቸው የጦፈ ክርክር ተነሳ።+ 25 እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “የአሕዛብ ነገሥታት በእነሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ፤ እንዲሁም በሕዝባቸው ላይ ሥልጣን ያላቸው ሰዎች በጎ አድራጊዎች ተብለው ይጠራሉ።+ 26 እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ።+ ከዚህ ይልቅ ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነ እንደ ታናሽ ይሁን፤+ አመራር የሚሰጥም እንደ አገልጋይ ይሁን።