13 ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለማዳን እባክህ ፈቃደኛ ሁን።+
ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+
14 ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ሁሉ፣
ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።
በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙ
አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።
15 “እሰይ! እሰይ!” የሚሉኝ
በሚደርስባቸው ኀፍረት የተነሳ ክው ይበሉ።
16 አንተን የሚፈልጉ+ ግን
በአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ።+
የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣
ምንጊዜም “ይሖዋ ታላቅ ይሁን” ይበሉ።+
17 እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤
ይሖዋ ትኩረት ይስጠኝ።
አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤+
አምላኬ ሆይ፣ አትዘግይ።+