1 ሳሙኤል 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋ ያደኸያል፤ እንዲሁም ያበለጽጋል፤+እሱ ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል።+ ዳንኤል 2:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 እሱ ጊዜያትንና ወቅቶችን ይለውጣል፤+ነገሥታትን ያስወግዳል፤ ደግሞም ያስቀምጣል፤+ለጥበበኞች ጥበብን፣ ለአስተዋዮችም እውቀትን ይሰጣል።+ ዳንኤል 4:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ይህ ነገር በጠባቂዎች ታውጇል፤+ የፍርድ ውሳኔውም በቅዱሳኑ ተነግሯል፤ ይህም ልዑሉ አምላክ በሰው ልጆች መንግሥት ላይ እንደሚገዛ+ እንዲሁም መንግሥቱን ለወደደው እንደሚሰጥና ከሰዎች ሁሉ የተናቀውን እንደሚሾምበት በሕይወት ያሉ ሁሉ ያውቁ ዘንድ ነው።” ሉቃስ 1:52 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 52 ኃያላን ሰዎችን ከዙፋናቸው አውርዷል፤+ ዝቅ ያሉትንም ከፍ አድርጓል፤+
17 ይህ ነገር በጠባቂዎች ታውጇል፤+ የፍርድ ውሳኔውም በቅዱሳኑ ተነግሯል፤ ይህም ልዑሉ አምላክ በሰው ልጆች መንግሥት ላይ እንደሚገዛ+ እንዲሁም መንግሥቱን ለወደደው እንደሚሰጥና ከሰዎች ሁሉ የተናቀውን እንደሚሾምበት በሕይወት ያሉ ሁሉ ያውቁ ዘንድ ነው።”