ዘዳግም 10:17, 18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የአማልክት አምላክና+ የጌቶች ጌታ እንዲሁም ታላቅ፣ ኃያል፣ የሚያስፈራ፣ ለማንም የማያዳላና+ ጉቦ የማይቀበል አምላክ ነው። 18 አባት ለሌለው* ልጅና ለመበለት ይፈርዳል፤+ እንዲሁም የባዕድ አገሩን ሰው ይወደዋል፤+ ምግብና ልብስም ይሰጠዋል። መዝሙር 146:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሖዋ የባዕድ አገር ሰዎችን ይጠብቃል፤አባት የሌለውን ልጅና መበለቲቱን ይደግፋል፤+የክፉዎችን ዕቅድ ግን ያጨናግፋል።*+ ዕብራውያን 13:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ስለዚህ በሙሉ ልብ “ይሖዋ* ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።+
17 ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የአማልክት አምላክና+ የጌቶች ጌታ እንዲሁም ታላቅ፣ ኃያል፣ የሚያስፈራ፣ ለማንም የማያዳላና+ ጉቦ የማይቀበል አምላክ ነው። 18 አባት ለሌለው* ልጅና ለመበለት ይፈርዳል፤+ እንዲሁም የባዕድ አገሩን ሰው ይወደዋል፤+ ምግብና ልብስም ይሰጠዋል።