ዘፀአት 9:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ሆኖም ኃይሌን እንዳሳይህና ስሜ በመላው ምድር እንዲታወጅ ስል በሕይወት አቆይቼሃለሁ።+ ኢሳይያስ 52:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ይሖዋ በብሔራት ሁሉ ፊት ቅዱስ ክንዱን ገልጧል፤+የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ የአምላካችንን የማዳን ሥራዎች* ያያሉ።+ ዳንኤል 3:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ስለዚህ በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ ማንኛውንም መጥፎ ነገር የሚናገር ከየትኛውም ብሔርና ቋንቋ የሆነ ሕዝብ ሁሉ እንዲቆራረጥ፣ ቤቱም የሕዝብ መጸዳጃ* እንዲሆን አዝዣለሁ፤ እንደ እሱ ማዳን የሚችል ሌላ አምላክ የለምና።”+ ዳንኤል 6:26, 27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 በየትኛውም የመንግሥቴ ግዛት የሚኖሩ ሰዎች የዳንኤልን አምላክ ፈርተው እንዲንቀጠቀጡ ትእዛዝ አስተላልፌአለሁ።+ እሱ ለዘላለም የሚኖር ሕያው አምላክ ነውና። መንግሥቱ ፈጽሞ አይጠፋም፤ የመግዛት ሥልጣኑም* ዘላለማዊ ነው።+ 27 እሱ ይታደጋል፤+ ደግሞም ያድናል፤ በሰማያትና በምድርም ተአምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን ያደርጋል፤+ ዳንኤልን ከአንበሶች መዳፍ ታድጎታልና።”
29 ስለዚህ በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ ማንኛውንም መጥፎ ነገር የሚናገር ከየትኛውም ብሔርና ቋንቋ የሆነ ሕዝብ ሁሉ እንዲቆራረጥ፣ ቤቱም የሕዝብ መጸዳጃ* እንዲሆን አዝዣለሁ፤ እንደ እሱ ማዳን የሚችል ሌላ አምላክ የለምና።”+
26 በየትኛውም የመንግሥቴ ግዛት የሚኖሩ ሰዎች የዳንኤልን አምላክ ፈርተው እንዲንቀጠቀጡ ትእዛዝ አስተላልፌአለሁ።+ እሱ ለዘላለም የሚኖር ሕያው አምላክ ነውና። መንግሥቱ ፈጽሞ አይጠፋም፤ የመግዛት ሥልጣኑም* ዘላለማዊ ነው።+ 27 እሱ ይታደጋል፤+ ደግሞም ያድናል፤ በሰማያትና በምድርም ተአምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን ያደርጋል፤+ ዳንኤልን ከአንበሶች መዳፍ ታድጎታልና።”