መዝሙር 25:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይሖዋ ጥሩና ቀና ነው።+ ኃጢአተኞችን ሊኖሩበት የሚገባውን መንገድ የሚያስተምራቸው ለዚህ ነው።+ መዝሙር 145:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሖዋ ለሁሉም ጥሩ ነው፤+ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ይታያል። ሉቃስ 18:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ለምን ጥሩ ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከአምላክ በቀር ጥሩ የለም።+