መዝሙር 27:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ፤+ከጠላቶቼ ጥበቃ እንዳገኝ ቀና በሆነ መንገድ ምራኝ። መዝሙር 119:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ይሖዋ ሆይ፣ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፤+እኔም እስከ መጨረሻው እከተለዋለሁ።+ መዝሙር 143:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በአንተ ታምኛለሁና፣በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን ልስማ። ፊቴን ወደ አንተ አዞራለሁና፣*ልሄድበት የሚገባውን መንገድ አሳውቀኝ።+ ኢሳይያስ 54:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ልጆችሽም* ሁሉ ከይሖዋ የተማሩ ይሆናሉ፤+የልጆችሽም* ሰላም ብዙ ይሆናል።+