ኢሳይያስ 48:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 የሚቤዥህ፣ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦+ “የሚጠቅምህን ነገር* የማስተምርህ፣+ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህእኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።+ ዮሐንስ 6:45 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 45 ነቢያት በጻፏቸው ጽሑፎች ላይ ‘ሁሉም ከይሖዋ* የተማሩ ይሆናሉ’+ ተብሎ ተጽፏል። ከአብ የሰማና የተማረ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል። ያዕቆብ 1:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እንግዲህ ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤+ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ* ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤+ ይህም ሰው ይሰጠዋል።+
5 እንግዲህ ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤+ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ* ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤+ ይህም ሰው ይሰጠዋል።+