መዝሙር 127:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 127 ይሖዋ ቤትን ካልገነባ፣ግንበኞቹ የሚደክሙት በከንቱ ነው።+ ይሖዋ ከተማን ካልጠበቀ፣+ጠባቂው ንቁ ሆኖ መጠበቁ ከንቱ ድካም ነው። ምሳሌ 16:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የምታደርገውን ሁሉ ለይሖዋ አደራ ስጥ፤*+ዕቅድህም ሁሉ ይሳካል። ኢሳይያስ 26:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ሰላም ትሰጠናለህ፤+ምክንያቱም የሠራነውን ነገር ሁሉያከናወንክልን አንተ ነህ። 1 ቆሮንቶስ 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ስለዚህ ምስጋና የሚገባው የሚያሳድገው አምላክ እንጂ የሚተክለውም ሆነ የሚያጠጣው አይደለም።+