2 ነገሥት 6:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ከዚያም ኤልሳዕ “ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን ክፈትለት”+ በማለት ጸለየ። ይሖዋም ወዲያውኑ የአገልጋዩን ዓይኖች ከፈተ፤ እሱም አየ፤ እነሆ የእሳት ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች+ በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራማውን አካባቢ ሞልተውት ነበር።+ መዝሙር 34:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የይሖዋ መልአክ አምላክን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፤+ደግሞም ይታደጋቸዋል።+ ማቴዎስ 18:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በሰማይ ያሉት መልአኮቻቸው በሰማይ ባለው አባቴ ፊት ዘወትር ስለሚቀርቡ ከእነዚህ ከትናንሾቹ መካከል አንዱንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ።+
17 ከዚያም ኤልሳዕ “ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን ክፈትለት”+ በማለት ጸለየ። ይሖዋም ወዲያውኑ የአገልጋዩን ዓይኖች ከፈተ፤ እሱም አየ፤ እነሆ የእሳት ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች+ በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራማውን አካባቢ ሞልተውት ነበር።+