-
ዘኁልቁ 16:5-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ከዚያም ቆሬንና ግብረ አበሮቹን ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “ጠዋት ላይ ይሖዋ የእሱ የሆነውን፣+ ቅዱስ የሆነውንና ወደ እሱ መቅረብ የሚችለውን+ ሰው ያሳውቃል፤ እሱ የመረጠውም+ ሰው ወደ እሱ ይቀርባል። 6 ስለዚህ እንዲህ አድርጉ፦ ቆሬ፣ አንተም ሆንክ ግብረ አበሮችህ+ በሙሉ የዕጣን ማጨሻዎች+ ውሰዱ፤ 7 ከዚያም በነገው ዕለት እሳት ካደረጋችሁባቸው በኋላ በይሖዋ ፊት ዕጣን ጨምሩባቸው፤ ይሖዋ የሚመርጠውም ሰው፣+ እሱ ቅዱስ ይሆናል። እናንተ የሌዊ ልጆች፣+ በጣም አብዝታችሁታል!”
-