ኢዮብ 28:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ሰውንም እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፣ ይሖዋን መፍራት ጥበብ ነው፤+ከክፉም መራቅ ማስተዋል ነው።’”+ ምሳሌ 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋን መፍራት* የእውቀት መጀመሪያ ነው።+ ጥበብንና ተግሣጽን የሚንቁት ሞኞች ብቻ ናቸው።+ መክብብ 12:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ሁሉ ነገር ከተሰማ በኋላ መደምደሚያው ይህ ነው፦ እውነተኛውን አምላክ ፍራ፤+ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፤+ ይህ የሰው አጠቃላይ ግዴታ ነውና።+