መዝሙር 72:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ክብራማ ስሙ ለዘላለም ይወደስ፤+ምድርም ሁሉ በክብሩ ትሞላ።+ አሜን፣ አሜን። መዝሙር 86:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ የሠራሃቸው ብሔራት ሁሉ ይመጣሉ፤በፊትህም ይሰግዳሉ፤+ለስምህም ክብር ይሰጣሉ።+ ኢሳይያስ 59:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 በፀሐይ መግቢያ ያሉ የይሖዋን ስም ይፈራሉ፤በፀሐይ መውጫም ያሉ ክብሩን ይፈራሉ፤እሱ የይሖዋ መንፈስ እንደሚነዳውኃይለኛ ወንዝ ሆኖ ይመጣልና። ሚልክያስ 1:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ* ድረስ ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል።+ በየቦታው ለስሜ የሚጨስ መሥዋዕትና መባ ተቀባይነት ያለው ስጦታ ሆኖ ይቀርባል፤ ምክንያቱም ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
11 “ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ* ድረስ ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል።+ በየቦታው ለስሜ የሚጨስ መሥዋዕትና መባ ተቀባይነት ያለው ስጦታ ሆኖ ይቀርባል፤ ምክንያቱም ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።