ዘፀአት 15:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 አዳኜ ስለሆነልኝ ያህ* ብርታቴና ኃይሌ ነው።+ እሱ አምላኬ ነው፤ አወድሰዋለሁ፤+ የአባቴ አምላክ ነው፤+ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።+ መዝሙር 18:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና ታዳጊዬ ነው።+ አምላኬ የምሸሸግበት ዓለቴ ነው፤+ጋሻዬ፣ የመዳኔ ቀንድና* አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው።+ ኢሳይያስ 12:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እነሆ፣ አምላክ አዳኜ ነው!+ በእሱ እታመናለሁ፤ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም፤+ያህ* ይሖዋ ብርታቴና ኃይሌ ነው፤ለእኔም አዳኝ ሆኖልኛል።”+