1 ነገሥት 3:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ስለሆነም አገልጋይህ ሕዝብህን መዳኘት እንዲሁም መልካምና ክፉ የሆነውን ነገር መለየት+ እንዲችል ታዛዥ ልብ ስጠው፤+ አለዚያማ ስፍር ቁጥር የሌለውን* ይህን ሕዝብህን ማን ሊዳኝ ይችላል?” ማርቆስ 11:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ በጸሎት የምትጠይቁትንና የምትለምኑትን ነገር ሁሉ እንዳገኛችሁት አድርጋችሁ እመኑ፤ ደግሞም ታገኙታላችሁ።+ 1 ዮሐንስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 እንዲሁም ትእዛዛቱን ስለምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኙትን ነገሮች ስለምናደርግ የምንጠይቀውን ሁሉ ከእሱ እንቀበላለን።+
9 ስለሆነም አገልጋይህ ሕዝብህን መዳኘት እንዲሁም መልካምና ክፉ የሆነውን ነገር መለየት+ እንዲችል ታዛዥ ልብ ስጠው፤+ አለዚያማ ስፍር ቁጥር የሌለውን* ይህን ሕዝብህን ማን ሊዳኝ ይችላል?”