መዝሙር 113:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 113 ያህን አወድሱ!* እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች፣ ውዳሴ አቅርቡ፤የይሖዋን ስም አወድሱ። ራእይ 19:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በተጨማሪም ከዙፋኑ የወጣ አንድ ድምፅ “እሱን የምትፈሩ ባሪያዎቹ ሁሉ፣+ ታናናሾችና ታላላቆች፣+ አምላካችንን አወድሱ” አለ።