መዝሙር 18:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና ታዳጊዬ ነው።+ አምላኬ የምሸሸግበት ዓለቴ ነው፤+ጋሻዬ፣ የመዳኔ ቀንድና* አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው።+ መዝሙር 84:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሖዋ አምላክ ፀሐይና+ ጋሻ+ ነውና፤እሱ ሞገስና ክብር ይሰጣል። ንጹሕ አቋም ይዘው የሚመላለሱትንይሖዋ አንዳች መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።+