45 ዳዊትም መልሶ ፍልስጤማዊውን እንዲህ አለው፦ “አንተ ሰይፍ፣ ጭሬና ጦር+ ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን አንተ በተሳለቅክበት፣+ የእስራኤል ተዋጊዎች አምላክ በሆነው በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ስም+ እመጣብሃለሁ። 46 ዛሬ ይሖዋ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጥሃል፤+ እኔም አንተን ገድዬ ራስህን እቆርጠዋለሁ፤ በዚህ ቀን የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ሬሳ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ በመላው ምድር የሚኖሩ ሰዎችም በእስራኤል አምላክ እንዳለ ያውቃሉ።+