ዘፀአት 19:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 አሁንም ቃሌን በጥብቅ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ መላው ምድር የእኔ ስለሆነ+ እናንተ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተመረጣችሁ ልዩ ንብረቶቼ* ትሆናላችሁ።+ ዘፀአት 31:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 እስራኤላውያን ሰንበትን መጠበቅ አለባቸው፤ በትውልዶቻቸው ሁሉ ሰንበትን ማክበር አለባቸው። ይህ ዘላቂ ቃል ኪዳን ነው። 17 በእኔና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ያለ ዘላለማዊ ምልክት ነው፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ሠርቶ በማጠናቀቅ ሥራውን ያቆመውና ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነው።’”+ ዘዳግም 4:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ዛሬ በፊታችሁ እንዳስቀመጥኩት እንደዚህ ሕግ ያለ የጽድቅ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ያሉት የትኛው ታላቅ ብሔር ነው?+ 1 ዜና መዋዕል 17:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 በምድር ላይ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ሌላ ብሔር ማን አለ?+ እውነተኛው አምላክ ሄዶ ሕዝቡ አድርጎ ዋጀው።+ ብሔራትን ከግብፅ ከዋጀኸው ሕዝብህ ፊት አባረህ+ ታላላቅና አስፈሪ ነገሮችን በመፈጸም ስምህን አስጠራህ።+ ሮም 3:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ታዲያ አይሁዳዊ መሆን ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው? ግርዘትስ ፋይዳው ምንድን ነው? 2 በሁሉም መንገድ ትልቅ ጥቅም አለው። በመጀመሪያ ደረጃ የአምላክ ቅዱስ ቃል+ በአደራ ተሰጥቷቸዋል።
16 እስራኤላውያን ሰንበትን መጠበቅ አለባቸው፤ በትውልዶቻቸው ሁሉ ሰንበትን ማክበር አለባቸው። ይህ ዘላቂ ቃል ኪዳን ነው። 17 በእኔና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ያለ ዘላለማዊ ምልክት ነው፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ሠርቶ በማጠናቀቅ ሥራውን ያቆመውና ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነው።’”+
21 በምድር ላይ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ሌላ ብሔር ማን አለ?+ እውነተኛው አምላክ ሄዶ ሕዝቡ አድርጎ ዋጀው።+ ብሔራትን ከግብፅ ከዋጀኸው ሕዝብህ ፊት አባረህ+ ታላላቅና አስፈሪ ነገሮችን በመፈጸም ስምህን አስጠራህ።+
3 ታዲያ አይሁዳዊ መሆን ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው? ግርዘትስ ፋይዳው ምንድን ነው? 2 በሁሉም መንገድ ትልቅ ጥቅም አለው። በመጀመሪያ ደረጃ የአምላክ ቅዱስ ቃል+ በአደራ ተሰጥቷቸዋል።