መዝሙር 49:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አፌ ጥበብን ይናገራል፤በልቤም የማሰላስለው ነገር+ ማስተዋልን ይገልጣል። መዝሙር 51:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ይሖዋ ሆይ፣ አፌ ምስጋናህን እንዲያውጅከንፈሮቼን ክፈት።+ መዝሙር 143:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የጥንቱን ዘመን አስታውሳለሁ፤ባከናወንካቸው ነገሮች ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤+የእጆችህን ሥራ በታላቅ ጉጉት አውጠነጥናለሁ።* ፊልጵስዩስ 4:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በመጨረሻም ወንድሞች፣ እውነት የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ቁም ነገር ያለበትን ነገር ሁሉ፣ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ በመልካም የሚነሳውን ነገር ሁሉ፣ በጎ የሆነውን ሁሉና ምስጋና የሚገባውን ነገር ሁሉ ማሰባችሁን* አታቋርጡ።+
8 በመጨረሻም ወንድሞች፣ እውነት የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ቁም ነገር ያለበትን ነገር ሁሉ፣ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ በመልካም የሚነሳውን ነገር ሁሉ፣ በጎ የሆነውን ሁሉና ምስጋና የሚገባውን ነገር ሁሉ ማሰባችሁን* አታቋርጡ።+