15 ዘወትር በጽድቅ የሚመላለስ፣+
ቅን+ የሆነውን ነገር የሚናገር፣
በማታለልና በማጭበርበር የሚገኝን ጥቅም የሚጠላ፣
ጉቦ ከመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣+
ደም ለማፍሰስ የሚጠነሰስን ሴራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን
እንዲሁም ክፉ የሆነውን ላለማየት ዓይኑን የሚጨፍን ሰው፣
16 በከፍታ ቦታዎች ይኖራል፤
ዓለታማ ምሽጎች አስተማማኝ መጠጊያው ይሆናሉ፤
ምግቡም ይቀርብለታል፤
የውኃ አቅርቦትም ፈጽሞ አይቋረጥበትም።”+