128 ይሖዋን የሚፈሩ፣
በመንገዱም የሚሄዱ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።+
2 በእጅህ ደክመህ ያፈራኸውን ትበላለህ።
ደስተኛ ትሆናለህ፤ ደግሞም ትበለጽጋለህ።+
3 ሚስትህ በቤትህ ውስጥ፣ ፍሬ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤+
ወንዶች ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ዛፍ ቡቃያዎች ይሆናሉ።
4 እነሆ፣ ይሖዋን የሚፈራ ሰው
እንደዚህ የተባረከ ይሆናል።+
5 ይሖዋ ከጽዮን ይባርክሃል።
በሕይወት ዘመንህ ሁሉ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ለማየት ያብቃህ፤+