መዝሙር 18:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ከብርቱ ጠላቴ አዳነኝ፤+ከእኔ ይበልጥ ብርቱዎች ከሆኑት፣ ከሚጠሉኝ ሰዎች ታደገኝ።+ መዝሙር 40:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤ይሖዋ ትኩረት ይስጠኝ። አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤+አምላኬ ሆይ፣ አትዘግይ።+ ምሳሌ 22:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ድሃውን ድሃ ስለሆነ ብቻ አትዝረፈው፤+ችግረኛውንም በከተማው በር ላይ ግፍ አትፈጽምበት፤+23 ይሖዋ ራሱ ይሟገትላቸዋልና፤+የሚያጭበረብሯቸውንም ሰዎች ሕይወት ያጠፋል።*
22 ድሃውን ድሃ ስለሆነ ብቻ አትዝረፈው፤+ችግረኛውንም በከተማው በር ላይ ግፍ አትፈጽምበት፤+23 ይሖዋ ራሱ ይሟገትላቸዋልና፤+የሚያጭበረብሯቸውንም ሰዎች ሕይወት ያጠፋል።*