መዝሙር 6:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሖዋ ሆይ፣ ዝያለሁና ሞገስ አሳየኝ።* ይሖዋ ሆይ፣ አጥንቶቼ ተንቀጥቅጠዋልና ፈውሰኝ።+ መዝሙር 41:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እኔም “ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ።+ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና+ ፈውሰኝ”*+ አልኩ። መዝሙር 51:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ያደቀቅካቸው አጥንቶች ደስ እንዲላቸው፣+የደስታንና የሐሴትን ድምፅ አሰማኝ።