መዝሙር 3:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ብዙዎች “አምላክ አያድነውም” እያሉ ስለ እኔ* ይናገራሉ።+ (ሴላ)* መዝሙር 42:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እንባዬ ቀን ከሌት ምግብ ሆነኝ፤ሰዎች ቀኑን ሙሉ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ይሳለቁብኛል።+ መዝሙር 79:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ብሔራት “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?+ በፈሰሰው የአገልጋዮችህ ደም የተነሳ የሚወሰድባቸውን የበቀል እርምጃ፣ዓይናችን እያየ ብሔራት ይወቁት።+