ዘዳግም 23:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 “ለአምላክህ ለይሖዋ ስእለት ከተሳልክ+ ለመፈጸም አትዘግይ።+ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በእርግጥ ከአንተ ይፈልገዋል፤ አለዚያ ኃጢአት ይሆንብሃል።+ መዝሙር 76:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ለአምላካችሁ ለይሖዋ ተሳሉ፤ ስእለታችሁንም ፈጽሙ፤+በዙሪያው ያሉ ሁሉ በፍርሃት ስጦታቸውን ያምጡ።+ መክብብ 5:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ለአምላክ ስእለት በምትሳልበት ጊዜ ሁሉ ስእለትህን ለመፈጸም አትዘግይ፤+ እሱ በሞኞች አይደሰትምና።+ ስእለትህን ፈጽም።+