1 ነገሥት 4:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 አምላክም ለሰለሞን እጅግ ታላቅ ጥበብና ማስተዋል እንዲሁም በባሕር ዳርቻ ላይ እንዳለ አሸዋ፣ ሰፊ ልብ* ሰጠው።+ ያዕቆብ 1:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን እወቁ፦ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየና+ ለቁጣ የዘገየ መሆን አለበት፤+