መዝሙር 101:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የባልንጀራውን ስም በስውር የሚያጠፋን ሰው፣+ጸጥ አሰኘዋለሁ።* ትዕቢተኛ ዓይንና እብሪተኛ ልብ ያለውን ሰው፣አልታገሠውም። ምሳሌ 8:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሖዋን መፍራት ማለት ክፉ ነገርን መጥላት ነው።+ ትዕቢትን፣ ኩራትን፣+ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ።+ ምሳሌ 16:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ይሖዋ ኩሩ ልብ ያለውን ሁሉ ይጸየፋል።+ እንዲህ ያለው ሰው ሳይቀጣ እንደማይቀር እርግጠኛ ሁን።