15 እሱ የማይታየው አምላክ አምሳልና+ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው፤+ 16 ምክንያቱም በሰማያትና በምድር ያሉ ሌሎች ነገሮች በሙሉ፣ የሚታዩትና የማይታዩት ነገሮች፣ ዙፋኖችም ሆኑ ጌትነት፣ መንግሥታትም ሆኑ ሥልጣናት የተፈጠሩት በእሱ አማካኝነት ነው።+ ሌሎች ነገሮች በሙሉ የተፈጠሩት በእሱ በኩልና+ ለእሱ ነው። 17 በተጨማሪም እሱ ከሌሎች ነገሮች ሁሉ በፊት ነው፤+ ሌሎች ነገሮች ሁሉ ወደ ሕልውና የመጡትም በእሱ አማካኝነት ነው፤