ምሳሌ 19:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ድሃን ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፤+ጓደኞቹማ ምን ያህል ይርቁት!+ እየተከታተለ ሊለማመጣቸው ይሞክራል፤ ምላሽ የሚሰጠው ግን የለም። ምሳሌ 30:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ውሸትንና ሐሰትን ከእኔ አርቅ።+ ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ። ብቻ የሚያስፈልገኝን ቀለብ አታሳጣኝ፤+ 9 አለዚያ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ከዚያም “ይሖዋ ማን ነው?” እላለሁ፤+ ደግሞም ድሃ ሆኜ እንድሰርቅና የአምላኬን ስም እንዳሰድብ* አትፍቀድ። መክብብ 7:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ገንዘብ ጥበቃ እንደሚያስገኝ+ ሁሉ ጥበብም ጥበቃ ታስገኛለችና፤+ የእውቀት ብልጫ ግን፣ ጥበብ የባለቤቷን ሕይወት ጠብቃ ማቆየት መቻሏ ነው።+
8 ውሸትንና ሐሰትን ከእኔ አርቅ።+ ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ። ብቻ የሚያስፈልገኝን ቀለብ አታሳጣኝ፤+ 9 አለዚያ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ከዚያም “ይሖዋ ማን ነው?” እላለሁ፤+ ደግሞም ድሃ ሆኜ እንድሰርቅና የአምላኬን ስም እንዳሰድብ* አትፍቀድ።