መዝሙር 39:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 እኔ “በምላሴ ኃጢአት እንዳልፈጽም+አካሄዴን እጠብቃለሁ። ክፉ ሰው ከእኔ ጋር እስካለ ድረስአፌን ለመጠበቅ ልጓም አስገባለሁ”*+ አልኩ። ምሳሌ 17:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 አዋቂ ሰው ንግግሩ ቁጥብ ነው፤+ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰውም የተረጋጋ ነው።*+ ምሳሌ 21:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ፣ራሱን ከችግር ይጠብቃል።*+ ያዕቆብ 1:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን እወቁ፦ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየና+ ለቁጣ የዘገየ መሆን አለበት፤+