ኢዮብ 28:28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ሰውንም እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፣ ይሖዋን መፍራት ጥበብ ነው፤+ከክፉም መራቅ ማስተዋል ነው።’”+ ምሳሌ 8:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሖዋን መፍራት ማለት ክፉ ነገርን መጥላት ነው።+ ትዕቢትን፣ ኩራትን፣+ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ።+ ኤርምያስ 32:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 ደግሞም ለእነሱ መልካም ነገር ከማድረግ እንዳልቆጠብ+ ከእነሱ ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ ከእኔም እንዳይርቁ በልባቸው ውስጥ እኔን የመፍራት መንፈስ አሳድራለሁ።+
40 ደግሞም ለእነሱ መልካም ነገር ከማድረግ እንዳልቆጠብ+ ከእነሱ ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ፤+ ከእኔም እንዳይርቁ በልባቸው ውስጥ እኔን የመፍራት መንፈስ አሳድራለሁ።+