ምሳሌ 12:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ሳይታሰብበት የሚነገር ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤የጥበበኞች ምላስ ግን ፈውስ ነው።+ ምሳሌ 16:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ደስ የሚያሰኝ ቃል እንደ ማር እንጀራ ነው፤ለነፍስ* ጣፋጭ፣ ለአጥንትም ፈውስ ነው።+ ምሳሌ 17:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 አዋቂ ሰው ንግግሩ ቁጥብ ነው፤+ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰውም የተረጋጋ ነው።*+