8 እንዲህም አልኳቸው፦ “ለብሔራት ተሸጠው የነበሩትን አይሁዳውያን ወንድሞቻችንን በተቻለን መጠን መልሰን ገዝተናቸው ነበር፤ ታዲያ እናንተ አሁን የገዛ ወንድሞቻችሁን መልሳችሁ ትሸጣላችሁ?+ ደግሞስ እንደገና ለእኛ መሸጥ ይኖርባቸዋል?” በዚህ ጊዜ የሚመልሱት ስለጠፋቸው ዝም አሉ። 9 ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፦ “የምትሠሩት ሥራ ጥሩ አይደለም። ጠላቶቻችን የሆኑት ብሔራት መሳለቂያ እንዳያደርጉን አምላካችንን በመፍራት መመላለስ አልነበረባችሁም?+